ሃተታ ዘ ካራማራ!

ሃተታ ዘ ካራማራ!
በኃይለማርያም ይርጋ
(ኢትዮጵያ ትቅደም!)
መንጌና ዝያድ ባሬ ራሳቸውን ማርክሲስት ሌሊኒስት ብለው የሰየሙ (self proclaimed) የሶቨየት ህብረት ጥገኛ ሃገር ሃገር (satellite state) መሪዎች ነበሩ። እንደውም ኢትዮጵያን፣ ደቡብ የመንን፣ ጅቡቲንና ሶማሌን ያቀፈ ማርክስሲስት ሌሊኒስት ኮንፌድሬሽን እንዲመሰርቱ ሃሳብ  ቀርቦ መንጌ ፈቃደኛ ሲሆን ዛይድ ባሬ ባለመስማማቱ ሳይሳካ ቀረ። ዝያድ  የታጠቀውን የራሽያና አሜሪካ ሰራሽ ዘመናዊ መሳሪያ ተማምኖ አዋሽ ድረስ ይዘልቃል ድንበሬ ብሎ ወረራ ጀመረ።

ትጥቅ አልባው መንጌ….

መንጌ የታጠቀው አብዛኛው ከጣልያን ጦርነት የተረፈ ሞይዘር፣ አልቤንና ምንሽር ነበር። ጀነራል አማን አምዶም (የኔ ጀግና) ከኪሲንጀር ጋር በጓዳዌ ስሜት(ሁለቱም የኮሪያ ዘማች ናቸዋ!)  ደብደቤ ተፃፅፎ ኮንግረሱ ቀጥታ የመሳሪያ ድጋፍ የሚከለክል ህግ ቢያወጣም እንደምንም በዱቤ የመቶ ሚሊየን ዶላር ጦር መሳሪያ ፈቀዱለት። ይህ መሳሪያ መሳሪያ መርከብ ላይ ተጭኖ ጉዞ ሊጀምር ሲል መንጌ ጀነራሉን ጨምሮ እነዛን የሃገር ባለውለታዎች ላይ  አብዮታዊ እርምጃ ወሰድኩ ብሎ አወጀ😭…ሰብዓዊ መብት ተቀዳሚ የወጭ ጉዳይ ፓሊሲው የነበረው የፕሬዝዳንት ከርተር አስተዳደር ጦር መሳሪያውን ከመርከብ ላይ አራግፎ፣ አስቀረው።

የኛ ሰዎችም የገዛነውን መሳሪያ ከለከሉን ብለው አስወሩ። አሁንም ብዙ ሰው እምነቱ ይኸው ነው።

መንጌም በግልፅ የሶቭየት ጎራ መቀላቅሉን በይፋ አወጀ። ወደ ሶቭየት በሮ ቤርዜኔቭ ጋር በሸናና ብሎ ፅዋውን አጋጭቶ ጨለጠ። ፍላጎቱን ጠየቁት፣ የሚፈልገውን የመሳሪያ አይነት ዘርዝሮ እሳወቁ። ይሁን አሉ።

አሜሪካኖች ይባስ ብለው በቀጠናው የሃይል ሚዛኑ (power balance) ለመጠበቅ  በተዘዋዋሪ ዝያድ ባሬን ደገፉ። ለምን ? ሌላ ጊዜ።  የሆኖ ሆኖ  ዘመናዊ መሳሪያ አልነበረም ሳይሆን ከጥላትህ ጋር አቻ የሚያደርግህ ጥራትና ብዛት ያለው መሳሪያ አልነበረም። አሜሪካ የሰለጠኑ ምርጥ መኮንኖች ነበሩት።  መንጌ ስልጣኑን ጠቅሎ አልያዘም ነበር፣ ሽግግር ላይ ስለነበር በውስጥ ጉዳይ ተወጥሮ ነበር።

ሶቨየት ስለምን ረዳችን?

በዚህ ወቅት ሶቨየት ህብረት ከሁለት አንዱን መምረጥ ነበረባት። ከርዕዮተ ዓለም ይልቅ አካባቢያዊ ጥቅም(strategic interest) የሚያስከብርልኝ የቱ ነው ብላ ገምግማ  በህዝብ ብዛት በአስር እጥፍ የምትበልጠውንና በቀይ ባህር አቋርጦ የሚያልፈውን የነዳጅ ጫኝ መርከብ ለመቆጣጠር የሚያስችላትን ምቹ መልክአምድር ያላት ኢትዮጵያን መረጠች፣ መንጌንም አይዞህ አለሁልህ አለችው ይለናል ክርስቶፎር አንድሪው  The World Was Going Our Way: The KGB and the Battle for the Third World በተሰኘው መፅሃፉ። ቀይባህር እንዲህ ጠቅሞን ነበር😢 አባይና የጣና ሃይቅም ጆኦፓለቲካዊ ፋይዳውም ቀላል አልነበረም።  አሁን ያለን የህዝብ ብዛት ወሳኝ አቅማችን( hard power) እንደሆን ልብ ይሏል፣ ሸማች ነዋ። 

ዝግጅት በመንጌ በኩል..

መንጌ ይርጋ ዱባለን፣ ጥሌን እና ሜሪ አርሚዴን ይዞ “የፍየል ወጠጤ”፣ “እኔስ ለሃገሬ” እያስጨፈረ ህዝቡን ከጫፍ ጫፍ አነቃንቆ ከሶስመቶ ሺ በላይ ሚሊሻና መደበኛ ወታደር አሰለጠነ፣ ግን ወቅቱ የሚጠይቀውን ዘመናዊ መሳሪያ አልያዘም ነበር። አንዳንድ ፊልሞችን አይታችሁ እንደሆን ሰልጣኞች ከጣውላ የተሰራ ጠመንጃ መሳይ ይዘው ልምምድ ሲያደርጉ የነበረው። ምን ተሻለ? ሶቨየት ህብረት ከላይ እንደገለፅኩት ከጥቅሟ አንፃር  ኩባንና ምስራቅ ጀርመን አስተባብራ በነፍስ ደረሰችልን።

ተዓምራዊው ርብርብ..

ለሶስት ወር ያህል የራሽያ የጦር አውሮፕላኖች መሳሪያ ጭነው #በየሃያ ደቂቃው የኢትዮጵያን መሬት ይረግጡ ነበር፣ ይለናል ክርስቶፎር አንድሪው ከላይ በተገለፀው መፅሃፉ ።  225 አውሮፕላኖች በማጓጓዙ ሂደት ተሳትፈዋል። 17,000 የኩባ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አንድ ሺ የሚሆኑ የራሽያ የጦር አማካሪዎች ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። 400 በመረጃ ደህንነት እና የጦር ምህንድስና የሰለጠኑ የምስራቅ  ጀርመን ወታደሮችም በረው ደርሰዋል።

ወደ ፍልሚያው

እንደ ዝያድ ባሬ መሳሪያ ቢታጠቁት ምን ይበጃል ከሃገር ፍቅር ስሜት እና ውኔ የተሞላ የመዋጋት ፍላጎ (The will to fight)  ከሌለው፣ ኢትዮጵያኖች ግን በዚህ አይታሙም። ሁሉም በሚችለው ተረባረበ። የአሪሲ እናቶች ከቀን ተሌት ገብስ ቆልተውና ፈጭተው በቅቤ ያበደ  አስራ አራት ኢነትሬ ከነተሳቢ ጭቆ አዘጋጅተው እንዳቀረቡ ከአንድ ጋዜጠኛ ሰምቻለሁ። ዛይድ ባሬ በመጣበት ድባቅ ተመትቶ በዚች እለት በካራማራ ተሰናበተ። ይህ ድል ሁሉም የኢትዮጵያ የፓለቲካ ሃይሎች ተሳትፈውበታል በተለይም መኢሶን ድርሻው ትልቅ ነበር። ኢሕአፓ ይታማል። ድሉ ግን የሁሉም ነበር!

የፍየል ወጠጤ ልቡ ያበጠበት፣
እንዋጋ ብሎ ለነብር ላከበት
..

ለ… ውዲቷ ለእናት ኢትዮጵያ

ታጥቄ

ጠንክሬ

የምሰዋላት ነኝ እኔስ ለሃገሬ

ጠ… ላቶቹዋን እቃወማለሁ

አጥብቄ

በብርቱ

ስለ ሀገር ፍቅር ገባኝ በእውነቱ
Eyob Dechasa  Nebyou Surafel ጓዶች እንኳን አደረሳችሁ!

Leave a comment